ከሞሮኮ ራባት የተነሳው ኮትዲቯራዊ የሠላም ተጓዥ ብስክሌተኛ ካቮሬ ካሪን 41 ሀገራትን አቆራርጦ 42ኛ መዳረሻው በሆነችው ኢትዮጵያ ተገኝቷል፡፡
ከዚህ በፊት ኢትዮጵያን በስም ብቻ ያውቃት እንደነበር ያስታወሰው የሠላም ተጓዡ÷ በአዲስ አበባ በተመለከተው ሁሉ መደነቁን እና መደሰቱን ተናግሯል፡፡
ጉዞውን ለማድረግ ምን እንዳነሳሳው ተጠይቆም እንደዚህ ዓይነት ጉዞ ሲያደርግ የመጀመሪያው መሆኑን በማስታወስ÷ “አኅጉር አቀፍ የሠላም ጉዞ ለማድረግ የወሰንኩት በአኅጉሪቱ ሠላም እንዲሰፍን ካለኝ ጥልቅ ፍላጎት የተነሳ ነው” ሲል መልሷል፡፡
ምንም እንኳን ጉዞው አስደሳች ቢሆንም በአንዳንድ ሀገራት ባለው የሠላም ችግር ምክንያት ለማለፍ ተቸግሬ ነበር ሲልም ገልጿል፡፡
በጉዞዬ ባለፍኩባቸው ሀገራት ሁሉ ልክ በሀገሬ እንዳለሁ ይሰማኝ ነበር፤ እኛ አፍሪካዊያን የሚያመሳስለን ነገር የሚበዛ አንድ ሕዝቦች መሆናችንንም ተመልክቻለሁ ብሏል፡፡
በኢትዮጵያ ቆይታውም ታሪካዊ ቦታዎችን እንደሚጎበኝ ነው የገለጸው፡፡
ከ42 ሀገራት ጉዞ በኋላ በስምንት የአፍሪካ ሀገራት ጉዞ እንደሚያደርግና ማጠናቀቂያውም ሞሮኮ መሆኑን አመላክቷል፡፡

No comments:
Post a Comment